ተነሳ ተራመድ[Tenesa Teramed] [Turkish translation]

Songs   2024-12-29 05:09:12

ተነሳ ተራመድ[Tenesa Teramed] [Turkish translation]

ወንዞች ይገደቡ ይዋሉ ለልማት

በከንቱ ፈሰዋል ለብዙ ሺ ዓመታት

ይውጡ ማእድናት ለሃገራችን ጥቅም

ህዝቧ ታጥቆ ይስራ በተቻለ ኣቅም

ተነሳ ተራመድ ክንድህን አበርታ

ላገር ብልፅግና ለወገን አለኝታ

ሀሁ ኢትዮጵያ ትቅደም

ሀሁ ኢትዮጵያ ትቅደም

ኢትዮጵያ ትቅደም

አሸብርቃ ታይታ በተፈጥሮ ሃብት

ተብላ እንዳነበር የአፍሪካ መሬት

ብለው እንዳልጠሯት የዳቦ ቅርጫት

እንዴት እናታችን ይጥማት ይራባት

ተነሳ ተራመድ ክንድህን አበርታ

ላገር ብልፅግና ለወገን አለኝታ

ተነሳ ተራመድ ክንድህን አበርታ

ላገር ብልፅግና ለወገን አለኝታ

ይቅር ማንቀላፋት ያበቃል መኝታ

ይትፋ ከሃገራችን ድህነት በሽታ

ይነገር ይለፈፍ ይታወጅ በይፋ

አንድነት ሃይል ነው የሁላችን ተስፋ

ተነሳ ተራመድ ክንድህን አበርታ

ላገር ብልፅግና ለወገን አለኝታ

ሀሁ ኢትዮጵያ ትቅደም

ሀሁ ኢትዮጵያ ትቅደም

ኢትዮጵያ ትቅደም

የእናት ሃገራችን ጥቃቷን አናይም

ህዝቧ ተበድሎ ማየት አንፈልግም

የዘር የሃይማኖት ልዩነት አንሻም

ይላሉ ልጆችሽ ኢትዮጵያችን ትቅደም

ተነሳ ተራመድ ክንድህን አበርታ

ላገር ብልፅግና ለወገን አለኝታ

ተነሳ ተራመድ ክንድህን አበርታ

ላገር ብልፅግና ለወገን አለኝታ

ሀሁ ኢትዮጵያ ትቅደም

ሀሁ ኢትዮጵያ ትቅደም

ኢትዮጵያ ትቅደም

Unknown Artist (Amharic) more
  • country:Ethiopia
  • Languages:Amharic
  • Genre:
  • Official site:
  • Wiki:
Unknown Artist (Amharic) Lyrics more
Excellent Songs recommendation
Popular Songs
Artists
Songs